የደቡብ አፍሪካ ያለፉት 20 ዓመታት ጉዞ ፍትህና እኩልነት በማረጋገጥ በአፓርታይድ ዘመን ተገልለው የነበሩ ዜጎች ተጠቃሚነት የጎለበተበት መሆኑን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጃኮቭ ዙማ ተናገሩ፡፡

 
የደቡብ አፍሪካ ያለፉት 20 ዓመታት ጉዞ ፍትህና እኩልነት በማረጋገጥ በአፓርታይድ ዘመን ተገልለው የነበሩ ዜጎች ተጠቃሚነት የጎለበተበት መሆኑን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጃኮቭ ዙማ ተናገሩ፡፡

የፕሬዝዳንት ጃኮቭ ዙማ ባዓለ ሲመት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በፕሪቶሪያ ተከብሯል፡፡
  
እና ሌሎች ተጨማሪ ዜናዎችን ይመልከቱ
 


በአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር መስመር ዝርጋታ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ በሚገኘው የአያት መገናኛ መስመር ላይ የተነጠፈው ሐዲድ፣ ከመሥፈርቱ ውጪ በመሆኑ ምክንያት በሌላ ሐዲድ በመቀየር ላይ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር መስመር ዝርጋታ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ በሚገኘው የአያት መገናኛ መስመር ላይ የተነጠፈው ሐዲድ፣ ከመሥፈርቱ ውጪ በመሆኑ ምክንያት በሌላ ሐዲድ በመቀየር ላይ ነው፡፡ ከሳምንት በፊት የተጀመረው ቀደም ሲል የተዘረጋውን ሐዲድ የመቀየር ሥራ በአሁኑ ወቅት ከአያት ወደ ሲኤምሲ አካባቢ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ የፕሮጀክቱ ኮንትራክተር የሆነውን ቻይና ሬልዌይ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንና የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ የሆነውን ስዌድሮድ የተባለ የስዊድን ኩባንያ ሪፖርተር ለማነጋገር ቢሞክርም፣ በኮንትራት ስምምነቱ መሠረት ለሚዲያ መግለጫ መስጠት እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ግን የፕሮጀክቱ ኮንትራክተር የመጀመሪያውን ሐዲድ የማንጠፍ ሥራ ሲጀምር፣ በኮንትራት ስምምነቱ ላይ በተቀመጡት መሥፈርቶች መሠረት እንዲሠራ ተነግሮት ነበር ብለዋል፡፡ በኮንትራት ስምምነቱ ላይ የተቀመጠው መሥፈርት አንዱ ባለ 25 ሜትር ሐዲድ ከሌላኛው ጋር የሚገናኘው በኦክስጅን ብየዳ እንደሆነ ቢገልጽም፣ ኮንትራክተሩ ግን የተቀመጠውን መሥፈርት እያወቀና በተቆጣጣሪ (አማካሪ) ድርጅቱ በተደጋጋሚ እየተነገረው ሐዲዱን መዘርጋት እንደቀጠለበት ምንጮች አስረድተዋል፡፡ አማካሪ ድርጅቱ ባለበት ኃላፊነት መሠረት ጉዳዩን ከማሳሰብ ባለፈ ለተዘረጋው ሐዲድ የሚቀርብ የክፍያ ጥያቄን እንደማያጸድቅ ግልጽ በማድረጉና በሌሎችም ምክንያቶች፣ ኮንትራክተሩ የስምምነት መሥፈርቱን ለማክበር እንደተገደደ ያስረዳሉ፡፡ ከአያት መገናኛ ባለው መስመር ላይ ተነጥፈው የነበሩት ሐዲዶች ብዛት 960 ሲሆኑ፣ እያንዳንዳቸው 25 ሜትር ርዝመት እንዳላቸው የሚያስረዱት ምንጮች፣ እየተነሱ ያሉት በመሥፈርቱ መሠረት መበየድ የማይችሉ ሆነው ስለተገኙ እንደሆነ ገምተዋል፡፡
‹‹ሙሉ በሙሉ መቀየር አለባቸው፡፡ ይህ ማለት ግን አገልግሎት አይሰጡም ማለት አይደለም፡፡ ምናልባት ከአዲስ አበባ ጂቡቲ ለሚዘረጋው የባቡር መስመር ሊያገለግሉ ይችላሉ፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡ አሁን ለተፈጠረው ችግር ምክንያቱ ኮንትራክተሩ እንደሆነ፣ ወጪውም ሙሉ በሙሉ የራሱ እንደሚሆን የሚያስረዱት ምንጮች፣ በዚህ ምክንያት የፕሮጀክቱ ጊዜ ተስተጓጉሏል ማለት እንደማይቻል ይገልጻሉ፡፡ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ ሐዲድ ማንጠፍ በዚህ ፕሮጀክት ላይ ቀላሉ የሥራ ዓይነት መሆኑን፣ በአጠቃላይ 34 ኪሎ ሜትሩ ላይ ሐዲድ የማንጠፍ ሥራ በአንድ ወር ማጠናቀቅ የሚቻል መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር በኃይሉ ስንታየሁ ተጠይቀው፣ የተነጠፈውን የሐዲድ መስመር የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ አፅድቆ እንዳልተረከበ ተናግረዋል፡፡ የኮንትራት ስምምነቱ የሐዲድ መስመሩ ‹‹ኮንቲኒየስሊ ዌልድድ›› ወይም አንድ የሐዲድ ብረት ከሌላኛው ጋር ያለምንም ክፍተት ተበይዶ መያያዝ እንዳለበት ያመለክታል ብለዋል፡፡ በመገናኛ አያት መስመር ላይ የተዘረጋው በዚህ መሠረት ሳይሆን ብሎን በማያያዝ በመሆኑና ይህ ደግሞ መሥፈርቱን የማያሟላ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ሪፖርተር በሥፍራው ተዘዋውሮ እንደተመለከተውና በፎቶግራፉ ላይም እንደሚታየው ቀደም ሲል የተነጠፉት ሐዲዶች እየተነሱ ነበሩ፡፡ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር በኃይሉ ግን፣ ‹‹እየተነሱ ያሉትን በማሳሰብና በማጠጋጋት ለመበየድ ነው እንጂ የሐዲድ ብረቶቹ እየተቀየሩ አይደሉም፤›› በማለት ያስተባብላሉ፡፡ የሐዲድ ማንጠፍ ሥራው ከመጀመሪያውኑ በመሥፈርቱ መሠረት ለምን በብየዳ አልተሠራም በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹መጀመሪያና መጨረሻ የሚባል ነገር በአሁኑ ወቅት የለም፡፡ እኛ ገና አልተረከብናቸውም፡፡ ምክንያቱም ገና ሒደት ላይ ነው ብለዋል፤›› ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል የተነጠፉትን ሐዲዶች በሌላ የመቀየር፣ እርስ በርስ የመበየድና የማያያዝ ተግባር በጐተራ መስመር ላይም መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ላይም የተጠየቁት ኢንጂነር በኃይሉ፣ የተነጠፉት ሐዲዶች እርስ በርስ ባልተበየዱባቸው ወይም በብሎን ብቻ በተያያዙባቸው ቦታዎች ላይ ሁሉ የመበየዱ ሥራ እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ቀላል የከተማ ባቡር ፕሮጀክት 34 ኪሎ ሜትር ሲሸፍን፣ ከምሥራቅ ምዕራብ እንዲሁም ከሰሜን ደቡብ የሚዘረጋ ነው፡፡ አጠቃላይ የፕሮጀክቱ ወጪ 475 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሆን ሲጠበቅ፣ ከጠቅላላ ወጪው 85 በመቶ የተገኘው ከቻይና መንግሥት በብድር ነው፡፡

የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና የሱዳን ባለሃብቶች ፌዴሬሽን ተባብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ አገር አቀፍ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና የሱዳን ባለሃብቶች ፌዴሬሽን ተባብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

የመግባቢያ ሰነዱ የሁለቱ አገራት ባለሃብቶችን በቅንጅት መሰራት የሚያስችላቸው ሲሆን በአገራቱ መካከል ያለውን ንግድና ኢንቨስትመንት ያሳድጋል።

ሰነዱ የተፈረመው በተባበሩት መንግስታት የስብሰባ ማዕከል የኢትዮ ሱዳን የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም በተካሄደበት ወቅት ነው።

የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት የአገር አቀፍ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ገብረሕይወት ገብረእግዚአብሔር እና የሱዳን ባለሃብቶች ፌዴሬሽን ኃላፊ ዋግዲ መረጋጊ ማህጉብ ናቸው።

የግሉ ዘርፍ በአገራቱ ንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች የጎላ ድርሻ እንዲኖረው ከማስቻል ባለፈ ባለሃብቶቹ ያላቸውን ልምድና ዕውቀት በመለዋወጥ በኩል ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል የአዲስ አበባ ዘርፍ ማህበራት ም/ቤቱ ፕሬዝዳንት፡፡

ዋግዲ በበኩላቸው የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ከቀረጥ ነፃ የንግድ ቀጣናንና የሱዳን ወደብን በጋራ በመጠቀም፣ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማቅረብና በቱሪዝም ዘረፍ ላይ በጋራ በመስራት ላይ ኢትዮጵያና ሱዳን የተፈራረሟቸውን ስምምነቶች መሰረት በማድረግ ባለሃብቶቹ በጋራ ለመስራት እንደሚያስችላቸው አስታውቀዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መብረሃቶም መለሰ በበኩላቸው የተፈረመው የመገባቢያ ሰነድ ወደ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚገቡትን ሱዳናውያን ባለሃብቶች ስለሚያሳድግ በአገሪቱ የኢንዱስትሪ ልማት ላይ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ትላንት ሌሊት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ከጥቅም ውጭ ሆነ ።

 
          አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) ትላንት ሌሊት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ከጥቅም ውጭ ሆነ ። በአደጋው በተወሰኑ ተማሪዎች ላይም መጠነኛ የአካል ጉዳት ደረሷል ።
የዩኒቨርሰቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አድማሱ ሽብሩ ለፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት እንደተናገሩት ፤ አደጋው ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ የተነሳ ሲሆን ፤ መንስኤው ግን እስካሁን ድረስ አልታወቀም ።
እሳቱን በአካባቢው ህብረተሰብና በአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪ ኤጀንሲ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር ማዋል ተችላል ያሉት ዶክተር አድማሱ ፤ አደጋው በሰው ህይወት ላይ ምንም ዓይነት ጎዳት አለማድረሱን ተናግረዋል።
በቃጠሎው ወቅት ከህንጻው ለመውጣት በሚያደረጉት ግፊያ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ተማሪዎች ከግድግዳ ጋር በመጋጨትና በመውደቅ ቆስለዋል።
 
ተማሪዎቹም በአካባቢው በሚገኝው አጣጥ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።